ከላይ በጠቀስኩት ርዕስ የምጽፍላችሁን ክስተት እጅግ በጥሞና አንብባችሁና ተረድታችሁ ገንቢ ሞያዊ አስተያየት እንድትሰጡበት አበክሬ እጠይቃለሁ ።
ነገሩ ወዲህ ነው። ልትወልድ በምጥ ላይ ያለች እናት በቀዶህክምና ለማዋለድ(Cesarean Section ) ወስኛለሁ! የህክምና ምክንያቴ ደግሞ ለማህፀን በር ማለስለሻነት የሰጠናት 25 ማይክሮ .ግ ሚሶፕሮስቶል ከመጠን በላይ ምጥ እንዲኖራት አድርጓል( (uterine contraction 7/10'(40-45)'' with unfavorable Bishop ) ;- በነገራችን ላይ ይህቺ እናት ወደሆስፒታላችን የመጣችሁ ከ40 ቀን በፊት የእንሽርት ውሀ ከግዜው ቀድሞ በመፍሰሱና ለ40ቀናት በጥብቅ ክትትል በሆስፒታላችን ቆይታለች(Preterm PROM)።
#ቀዶ_ ህክምና_ክፍል(OR)
ሀሉም ነገር ተጠናቆ ቀዶ ህክምና ክፍል ይዘናት ገባን ። ሁሌም እንደማደርገው የክፍሉን ሰራተኞች ሰላምታ ሰጥቼና ስለ ታካሚዬ ገለፃ በማድረግ ድንገተኛ ቀዶ ህክምና እንደሆነ አስረድቼ በፍጥነት እንዲዘጋጁ አደረኩ። በዚህ መሀል Scrub ነርሷ Assistant እንዲመጣና እርሷ እንደከዚህ ቀደም የሁለቱን ስራ እንደማትሰራ እየተበሳጨች ተናገረች ።እኔም ቀዶ ህክምናው በጣም ድንገተኛ መሆኑን ነግርያት ለጊዜው በአቅራቢያው Assistant ማግኘት እንደማይቻል አስረድቻት የሰመመን ባለሙያው መድሀኒቱን ለእናት ከሰጣት ቦኾላ ቀዶ ህክምናውን ጀመርን ። Skin>Facia >muscle >peritoneum >Uterus ,,,,,,የልጁን ጭንቅላት አገኘሁት :ለማዋለድ የቀረኝ ትንሽ ከላይ በኩል ገፋ የሚያደርግልኝ ሰው ነው (fundal),,,,Scrub ነርሷን ግፊልኝ አልኳት #አልገፋም_ አለችኝ! ,,,ኧረ ግፊ ! እሷው 'አልገፋም',,,,ኧረ ግፊ የሰው ልጅ ይሞታል! እሷ 'አልገፋም' ስራዬ አይደለም ,,,በዚህ መሀል ራሴን በመቆጣጠር,,,ልጅ ልትቀበል የገባችሁን ሚድዋይፍ (Non sterile )ጓንት አድርጋ ከላይ እንድትገፋ አድርጌ ልጁን ማዋለድ ብንችልም 'በግፊ አልገፋም' ሰጥአገባ ልጁ መጠነኛ መጎዳት አጋጥሞት ወደህጻናት ክፍል ሲገባ እናትም ከሚገባው በላይ ልትደማ ችላለች።
1ኛ. እኔ ምን ማድረግ ነበረብኝ
2ኛ. በድንገተኛ ቀዶ ህክምና ወቅት አንድ ባለሞያ ማድረግ የሚችለውን ነገር ስራዬ አይደለም በሚል አለማድረግ ይችላል?
3ኛ.የከፋ ነገር ቢገጥምና እናትና ልጅ ለአደጋ ቢጋለጡ ህጉ ምን ይላል?
ሀሳብ ስጡበት!
በኢትዮጵያ ከሚገኝ አንድ ጠቅላላ ሆስፒታል
S.T
#ለጥያቄህ_መልስ እነሆ!
#1:- እኔ ምን ማድረግ ነበረብኝ?
አንድ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የመስጠት ብቃት አለው የሚባለው (የሥራ ፈቃድ የሚያገኘው) በሰው ኃይል (professional)፣ በግቢው+ ሕንፃው+ ግብዓት (premise)፣ በሚሰጠው አገልግሎት (product/service) እና በአሠራር ሥርዓቱ (process) ቢያንስ ዝቅተኛውን ደረጃ minimum standard ማሟላት ሲችል ነው። ሁሉ ነገር ሁሌ ሊሟላ እንደማይችል ግልፅ ቢሆንም የሆስፒታሉ ኃላፊዎች የሥራው ሂደት እንዳይስተጓጎል የጎደለውን በቶሎ እያሟሉ ሥራው እንዲቀጥልና ታካሚ ላይም ጉዳት እንዳይደርስ የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ሆስፒታሉ ዝቅተኛውን መስፈርት ባለማሟላቱ ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊነት አለበት (ለምሳሌ በቂ ባለሙያ ባለመኖሩ ምክንያት ታካሚዋ ወደ ሌላ ቦታ በቅብብሎሽ referral ተልካ መዘግየት delay ቢፈጠርና ጉዳት ቢደርስ)። ከዚህ አኳያ አንተ የቀዶ ሕክምና ለማድረግ ከመወሰንህ በፊት ሆስፒታሉ የሚያስፈልገውን ባለሙያም ሆነ ግብዓት ማሟላቱን ማረጋገጥ ነበረብህ። ይኽን ከግንዛቤ ባለማስገባት ቀዶ ሕክምና ለማድረግ መወሰንህ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በግል እንድትወስድ ያደርግሃል።
2:-…